Ethiopians Fun Forum.
Would you like to react to this message? Create an account in a few clicks or log in to continue.
Log in

I forgot my password

Who is online?
In total there are 3 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 3 Guests

None

[ View the whole list ]


Most users ever online was 156 on Mon Mar 15, 2021 10:19 am
New Sites
አዲስ ሳይት

ኢትዮ ሲንግልስ
Meet Ethiopians Singles | Register Now

ኢትዮ ፎረም
Ethiopians Forum
Latest topics
» Sh\\a Sex{wl
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyThu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyThu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyThu Oct 23, 2014 5:12 pm by nenash

» Sxs Film Hindi
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyTue Oct 21, 2014 9:31 pm by nenash

» Kingdom Age Hack Tool V2.5
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyTue Oct 21, 2014 8:00 am by nenash

» Ore Wa Kanojo O Shinjiteru! 02 | Checked
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyMon Oct 20, 2014 3:57 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySun Oct 19, 2014 2:20 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySun Oct 19, 2014 2:17 pm by nenash

» Hide My Ip Activation Key 5.4
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySun Oct 19, 2014 11:14 am by nenash

» Windows 8 All Editions Activator.exe
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySat Oct 18, 2014 10:01 pm by nenash

» ?????? Anime Anime03 ?? ?? ?? ???? ?? Blu-ray?
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySat Oct 18, 2014 8:08 pm by nenash

» Rhcsa Rhce Red Hat Linux Certification Practice Exams With V
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySat Oct 18, 2014 6:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySat Oct 18, 2014 12:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptySat Oct 18, 2014 12:05 pm by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyThu Oct 16, 2014 1:20 am by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyThu Oct 16, 2014 1:16 am by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyWed Oct 15, 2014 9:31 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyWed Oct 15, 2014 9:24 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyWed Oct 15, 2014 9:23 pm by nenash

» [Most_popular]_tudung_bj_abg_opis_3gp-adds
Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? EmptyWed Oct 15, 2014 1:06 pm by nenash


Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

2 posters

Go down

Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? Empty Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Post by yaredlove Sun Oct 04, 2009 6:20 am

የአክሱም የንግድ መረብ

ፊሊፕሰን የተሰኙ ፀሐፊ አንድ የአክሱሞች ንጉሥ ምናልባትም ኢዛና ሊሆን ይችላል፡፡ በ340 ዓ.ም. አካባቢ ከምዕራብ አክሱም እስከ ሽሬ ግዛት ወደ ግብጽ መንገድ መዘርጋቱንና ይህንንም ያደረገው መውጫውን ለማስከበር ንግድን ለመቆጣጠርና የንግድን መስመር ወደ ምዕራብና ሰሜን ለመዘርጋት አስቦ እንደሆነ በ2002 ጽፈዋል፡፡ ይህ የንግድ መረብ አክሱምን በተጨማሪ ትልቅ ከተማ እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ለማየት ያስችላል፡፡

(የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት፣ አክሱም ለምን?፣ 2000)

-------------------------------------------------------------------

የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ

በየጊዜው የሚሠሩት አውሮፕላኖች በፍጥነታቸው፣ በሚያቋርጡት ርቀት በሚጭኑት መሣሪያ እየላቁና እየተራራቁ ሄደው በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የነበሩት አውሮፕላኖች ከ500 ኪ.ሜ በላይ ፍጥነት ያልነበራቸው ሲሆኑ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ግን ከ6500 ኪ.ሜ በላይ አቋርጠው የሚሄዱ፣ ከ10"000 ኪሎ ግራም የማያንስ መሣሪያ የሚጭኑና ከ500-800 ኪ.ሜ በሰዓት የሚጓዙ ሆነው ተሠሩ፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለቂያ አንስቶ እስካሁን አለንበት ጊዜ ደግሞ ማለትም የመጀመሪያው በረራ በተደረገ በ77 ዓመት የሚጭኑት መሣሪያ በቶን የሚቆጠር፣ ለሚያቋርጡት ርቀት ወሰን የሌላቸው (አየር ላይ ነዳጅ በመሙላት) ፍጥነታቸው ከድምጽ ፍጥነት በሦስት እጅ የሚበልጡ. በሬዲዮ የሚመሩ መሣሪያዎች ያሏቸውና የአንደኛው ወገን የሌላውን ከኢላማው ሳይደርስ ለማጨናገፍ የሚያስችሉ ናቸው፡፡

(መኮንን በሪ፣ አቪየሽን፣ 1995)
-----------------------------------------------------------------------
መስከረም

መስከረም፡- ከረመ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ቀዳማይ፣ ለዓለም ሁሉ መጀመሪያ፣ ርእሰ ክራማት፣ መቅድመ አውራኅ ማለት ነው፡፡ መስከረም፡- ዐውደ ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው ማለትም ይሆናል፡፡



መስከረም በክረምት ውስጥ የሚካተት ቢሆንም የጨለማው ጊዜ አልፎ ብርሃን የሚታይበት፣ ዕፅዋትና አዝርእት የሚያብቡበትና የሚያፈሩበት፣ እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሣር እየነጩ የሚቦሩቁበት፣ በአጠቃላይ ምድር በአበቦች የምታጌጥበት፣ ሰማይ የደመና ቡሉኮውን (ጋቢዋን) ጥሎ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊት በከዋክብት ማጌጥ የሚጀምርበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ወር ናት፡፡

የመስከረም ስም ሲነሣ በግንባር ቀደምነት የሚወሱት አበባና እሸት ናቸው፡፡ በተለይ አበባ ከመስከረም ጋር ያላት ትስስር የተለየ ነው፡፡ አበባ በጥቅምትም ያለ ቢሆንም መስከረምን ያለ አበባ፣ አበባን ያለ መስከረም ማሰብ ያለ ደመና ዝናብ ለማግኘት የመመኘት ያህል ነው የሚሆነው፡፡ ከነተረቱ "መስረከረም በአበባው ሰርግ በጭብጨባው" እንዲሉ፡፡

"እንቁጣጣሽ" በኢትዮጵያ ብቻ የምትገኝ (የምትበቅል) ከመስከረም መጀመሪያ እስከ መስቀል ባለው ጊዜ የምታብብ ውቡ አበባ ናት፡፡ በትግራይ "ገልገለ መስቀል" እየተባለች ነው የምትጠራው፡፡ ደቡብ ጐንደሮች ደግሞ "አጐሮጐምባሽ" እያሉም ይጠሩዋታል፡፡ በመስከረም የምታብበው ግን እንቁጣጣሽ ብቻ አይደለችም፡፡ የድመት ዐይን፣ የጅብ ጫማ፣ አደይ አበባ፣ የልጃገረድ ኩል የመሳሰሉት በመስከረም ወር ብቻ ከሚያብቡ የአበባ ዓይነቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ሌላው የመስከረም መለያ፣ እሸት ነው፡፡ በሀገራችን ቆላማ አካባቢዎች እሸት የሚደርሰው ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ እሸት ከቅዱስ ዮሐንስ (እንቁጣጣሽ) በፊት አይቀመስም፡፡ ከዚሁ ከእሸት ጋር በተያያዘ መረሳት የሌለበት ጉዳይም አለ፡፡ በሀገር ቤት አዲስ ተጋቢዎች (ጐጆ ወጪዎች) በእንቁጣጣሽ የበቆሎ እሸት በስልቻ ሞልተው ለወላጆቻቸው ይወስዳሉ፡፡ ሌላውም ቢሆን እሸት ያለው ለሌላው "ዓመት ዓመት ይድገመን" እያለ ለጐረቤቱ እሸት ያድላል፡፡ ተቀባዮችም "እህል ይታፈስ ይርከስ፣ ሳቢ በሬውን አራሽ ገበሬውን ይባርክ፣ ኑሮአችሁ፣ ሕይወታችሁ እንደ እሸት የለመለመ ይሁን ወልዳችሁ ሳሙ ዘርታችሁ ቃሙ" እያሉ ይመርቁዋቸዋል፡፡
"እንቁጣጣሽ-አጐሮጐምባሽ"

ልጃገረዶች በእንቁጣጣሽ ማለዳ በየቤቱ እየዞሩና "እንቁጣጣሽ-አጐሮጐምባሽ" እያሉ የሚያድሉትን እንግጫና አበባ የሚቀጩት (የሚነቅሉት) በእንቁጣጣሽ ዋዜማ ምሽት ነው፡፡ ልጃገረዶቹ እንግጫ ነቀላ ወደ መስክ ሲሔዱ ወንዶች ችቦ ይዘው ያጅቡዋቸዋል፡፡ መስክ አንደ ደረሱ ለልጃገረዶቹ "አበባየሁ አበባየሁ አደይ" እያሉ እንግጫ መንቀል ሲጀምሩ ወንዶች ችቦዎቻቸውን ይዘው ፊት ለፊታቸው ቆመው ያበሩላቸዋል፡፡
(ካህሣይ ገ/እግዚአብሔር፤ ኅብር ብዕር፣ 1996)
__________________________________________________________


Last edited by yaredlove on Mon Oct 05, 2009 11:34 pm; edited 1 time in total
yaredlove
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 31
Location : Ethiopia/Nazareth

http://www.yared.tk

Back to top Go down

Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? Empty Did you know this?(part 2)

Post by yaredlove Sun Oct 04, 2009 6:29 am

ዲናሚት

እ.ኤ.አ 1833 ዓ.ም ተወልዶ 1896 ዓ.ም የሞተው ስዊድናዊው አልፍሬድ ቢርናርድ ኖቤል ድንጋዮችን በመፍለጥ አለቶችን በማፈራረስ ሌሎችንም ብዙ ነገሮች በመለያየት የነበረውን ብርቱ ድካም ለማስወገድ ብሎ ዲናሚት የተባለውን ፈንጂ አዘጋጀ፡፡ ሰዎች ግን ይህን ፈንጂ ነገር ለጦር መሣሪያነት አውለው ብዙ ሕዝቦችን ያለርኅራኄ ሲፈጁበት እና የዚህ ፈንጅ አግኝ የሆነው ኖቤል ለሰው ዘር ጥቅም ብሎ የሠራው ነገር የብዙ ንጹሕ ደም መፍሰሻ ሆኖ ስላየ በኃዘንና በፀፀት ሲሰቃይ ከኖረ በኋላ በሞቶ ጊዜ ያጠራቀመው ሀብት ሁሉ የሰውን ልጆች መንፈስ ወደ መልካም ነገር የሚመራና ከፍተኛ አስተያየት ያለው መጽሐፍ ለጻፈ ታላቅ ደራሲ የሰውን ልጆች በሽታ ድካምና ችግር ለማቃለል የሚጠቅም አዲስ ነገር ላገኘ የሳይንስ ሊቅ የሰው ልጆችን የሚያሰቃዩ ጦርነቶችና ስደቶች እንዳይደርሱ ሰላምና እርቅ ላስገኘ የሰላም ሰው ሽልማት እየሆነ እንዲሰጥ ተናዝዞ ሞተ፡፡

(አቤ ጎበኛ፣ አልወለድም፣ 1993)
-----------------------------------------------------------------------
ይድነቃቸው ተሰማ

ገና የ14 ዓመት አዳጊ ወጣት እያሉ በ1935 ዓ.ም በአገራችን የመጀመሪያው የስፖርት ክለብ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ሲቋቋም ለቀሪው ድንቅ የሕይወታቸው ጥሪ መንጠሪያ ይሆን ዘንድ ወደዚህ ቡድን ገቡ፡፡ ይህም ድልድይ ሆኗቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ በቁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኳስ ዕረፍታቸው፣ ኳስ ሽርሽራቸው፣ ኳስ ቀጠሯቸው ሁሉ፣ ኳስ ሜዳ ሆነ፡፡ ይድነቃቸው ክለባዊና አገራዊ የድርሻ ምዕራፎቻቸው የሚነበቡት 23 የእግር ኳስ ቡድንና ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1954 በ15 ጊዜያት በተሰለፉበት የብሔራዊ ቡድን ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች ተለይተው በመውጣት ታላቅ አገራዊና አህጉራዊ የስፖርት ዓለም አስተዋፅኦቸው የሚጀምረው ከእንዲህ ዓይነቱ የኳስ ተጫዋችነታቸው ምዕራፍ በኋላ ነው፡፡

(ሰሎሞን ጥላሁን፣ ደማቆቹ፣ 2000)
-----------------------------------------------------------------------
እርሳስ

ይህ ንጥረ ነገር በጣም ልል እና ከባድ በመሆኑ ይታወቃል፡፡ ከመደበኛ ብረታ ብረቶች መሀል በክብደት የሚበልጠው ወርቅ ብቻ ነው፡፡ እርሳስ በጣም ልል ከመሆኑ የተነሳ በቀላሉ በጥፍር ሊቧጨር ይችላል፡፡ ይህ ስጦታው ስላለም እርሳስ ቧንቧዎችን ለመስራት በጣም ተፈላጊ ሆነ፡፡ የጥንት ሮማውያን እርሳስን ለውሃ ማስተላለፊያና የሕዝብ መታጠቢያዎች ማካሄጃ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ እርሳስ በጣም ዝቅ ባለ ሙቀት ስለሚቀልጥ ለመበየጃም ይጠቀሙበት እንደነበር ይነገራል፡፡

አሁን ባለንበት ዘመን የአቶሚክ ኃይል አስፈላጊነት እያደገ በመሄዱ እርሳስ ከሰራጺ ጨረር (ራዲያዮሽን) እንደ ጋሻ እየሆነ በመከለል ስለሚረዳ ጠቃሚነቱ ታውቆለታል፡፡ ለምሳሌ ሰራፂ ጨረር የሚለቅቁት እንደ ዮራኒዬም ያሉት ንጥረ ነገሮች ጋማ የተባሉ ለሰው ልጅ አደገኛ የሆነ ጨረሮች ይለቅቃሉ፡፡ ታዲያ በእርሳስ ግርዶሽ ተጋርዶ እንደሆነ እነዚህ ጨረሮች ስለሚታገዱ ሰውን ከመጎዳት ይቆጠባሉ፡፡ እርሳስ እንዲሁም በየሆስፒታሎች የሚገኘውን ኤክስሬይ ጨረር ወይም ራጅ ጨረሩ አልፎ በሰውነት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በመጋረድ ይረዱናል፡፡ እርሳስ በተጨማሪም በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ድምጽ ሲቀረፅም ሆነ ሲተላለፍ ፀጥታ እንዲሰፍንና የውጭ ድምጽ እየገባ እንዳያውክ የሚጋርድና የሚረዳም ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በአነጋገር በተፈጠረው ስህተት እርሳስ ማለት ለምንጽፍበት እርሳስ ምንጭ አይደለም፡፡ የመጻፊያው እርሳስ ግራፍት ከተባለ ሌላ ንጥረ ነገር የሚሠራ ነው፡፡ የእርሳስ ዋናው ዘመናዊ አገልግሎት በመኪና ባትሪ ሥራ በኩል ነው፡፡

(ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ፣ ዓለም የሠራተኞች ናት)
yaredlove
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 31
Location : Ethiopia/Nazareth

http://www.yared.tk

Back to top Go down

Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? Empty Re: Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Post by girreda Sun Dec 20, 2009 7:43 am

ክቡር ሚኒስትር


(የዓለማችን የአየር ጠባይ ለውጥ ችግርን ለመፍታት የተባበሩት መንግሥታት በዴንማርክ ኮፐንሀገን ባዘጋጀው
ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ሉዑካን ተገኝተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩም እዚያው ናቸው፡፡ አፍሪካውያን ስብሰባውን ረግጠው ሲወጡ አብረው ወጥተዋል፡፡ አዘጋጆቹ ተደናግጠው እዚህም እዚያም አፍሪካውያንን እያነጋገሩ ናቸው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩንም ጭምር)
- ክቡር ሚኒስትር እንዴት ስብሰባ ረግጣችሁ ትወጣላችሁ?
- እንዴት አንወጣም? እኛኮ እዚህ የመጣነው የአፍሪካን ችግር ለማቃለል እንጂ አፍሪካን ለሞት ለመዳረግና ለእርድ ለማቅረብ አይደለም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እኛኮ የአፍሪካንና የዓለምን ጥቅም ለማስከበር ነው የምንሯሯጠው፡፡ የዓለም የዓየር ጠባይ እናሻሽል ስንልኮ ዓለም የሁላችንም መሆንዋን ስለምንገነዘብ ነው፡፡
- ሃሳባችሁ እንደዚያ ሊሆን ይችላል፡፡ ተግባራዊ እንቅስቃሴያችሁን ስናይ ግን የበለፀጉት አገሮችን ጥቅም ለማስከበርና የአፍሪካን ጥቅም ለመርገጥ ነው፡፡
- ቀስ በቀስ ሕጋዊ በሆነ መልኩ፣ ሁሉም በሚስማማበትና በሚፈራረምበት መንገድ ለመሄድ ስፈለግን ነውኮ፡፡
- ከአሁን በፊት ስምምነት ላይ ተደርሶበት የተፈረመ ውልና ስምምነት ለምን ትረግጣላችሁ?
- ምኑን?
- የሚረጭ የጋዝ መጠንን የሚወስን ውልና ስምምነት ነበር፡፡ እሱን ረግጣችሁና ወደጎን ትታችሁ ለምን ትሄዳላችሁ? የኪዮቶ ስምምነት መከበር አለበት፡፡
- አሜሪካውያኑ ስላልተስማሙበትና ስላልፈረሙበት ነውኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ታዲያ ያልፈረመውን እንዲፈርም ይደረጋል እንጂ የፈረመው አይረገጥም፡፡
- ምን መሰለዎት ክቡር ሚኒስትር? የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አፍሪካን ወክለው የሚናገሩና የሚደራደሩ ስለሆነ ኢትዮጵያ ከእኛ ጋር ብትሆን ጥሩ ነው፡፡
- የአፍሪካን ጥቅም ከሚያስከብር ጋር እንሆናለን፡፡ መመዘኛችንና እዚህ የመጣንበት ምክንያትም ይኸው ነው፡፡
- አንዴ ይቅርታ፡፡ ሰዎች ስለሚፈልጉኝ ልሂድ፡፡
(ክቡር ሚኒስትሩን የጠሯቸው የናይጄሪያ ዋና ተደራዳሪና የሱዳኑ ተከራካሪ ነበሩ፡ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር መከሩ፡፡ ስብሰባው የአፍሪካን ድምፅ የሚያዳምጥ ከሆነ እንደገና ወደ ስብሰባው እንደሚመለሱም ተስማሙ፡፡ ጂ 77 የተባለው የታዳጊ አገሮች ስብስብ ከጎናቸው እንደሆነ አረጋገጡ፡፡ ይህን መክረው እንደተለያዩ፣ ከበለፀጉት አገሮች የመጣ አንዱ ልዑክ ክቡር ሚኒስትሩ ጋ መጥቶ ማነጋገረ ጀመረ)
- ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ጤና ይስጥልኝ፡፡
- ከሱዳኑ ሰውዬ ጋር አብራችሁ ሳያችሁ እኮ ገርሞኝ ነው፡፡
- ለምን ይገርምሃል?
- ሱዳኖች በዳርፉር ብዙ ግፍ እየፈፀሙ ስለሆነና መሪያቸው አልበሽርም ስለሆነ ኢትዮጵያ ከእነሱ ጋር እንዴት ታወራለች ብዬ ነዋ፡፡
- ሃ...ሃ...ሃ
- ምነው ሳቁ ክቡር ሚኒስትር?
- የሳቅኩበት ምክንያትማ የሚያስቅ ነገር ስለተናገርክ ነው፡፡ የኢንቫይሮመንቱ እንዳይበቃን በዚህ ንግግርህም አፍሪካ ላይ ንቀት እያሳየህ ነው፡፡
- እንዴት ንቀት ክቡር ሚኒስትር?
- በዚህ ስብሰባ ላይ አፍሪካውያን አብረን ስለቆምን የሱዳን፣ የናይጄሪያ፣ የኢትዮጵያ ወኪሎች አብረው ቆመው ስለተከራከሩ በዳርፉር አጀንዳ ገብተህ ልትለያየን ፈለግክ አይደል?
- ለመለያየት አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ነው እንጂ፡፡ ይህ የሱዳን ሰውዬ ጎበዝና ጥሩ ሰው ነው፡፡ ተሟጋችና ተከራካሪ ነው፡፡ በስብሰባው ጥሩ ሃሳብ አቅርቧል፡፡ ዳርፉርን ምን አመጣው?
- ለሁሉም ነገር ዴሞክራሲ ወሳኝ ነው ብዬ ነው፡፡
- ቻይናን እየተለማመጣችሁ ያላችሁት ዴሞክራሲ ቻይና ውስጥ አለ ብላችሁ ነው?
(ሰውዬው ተናዶም ሄደ፡፡ በሩቅ ሆኖ ሲጠብቅ የነበረው አንድ ከቻይና የመጣ ልዑክ ወደ ክቡር ሚኒስትሩ መጣ)
- ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ ጥሩ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ ከጎናችሁ ነን፡፡
- እናመሰግናለን ግን...
- ግን ምን? ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ የበለፀጉት አገሮች ለአፍሪካ ካሳ ይከፍላሉ ብላ ያቀረበችው ሃሳብ ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን፡፡
- ጥሩ ነው
- እንዲያውም ከአፍሪካ ጎን ስለቆምን የታወቁት ያደጉት አገሮች ቅር ብሏቸዋል፡፡
- ጥሩ ነው ግን እናንተ ቻይናዎችምኮ "ክላይሜት"ን በሚመለከት ችግር አለባችሁ፡፡
- ምን ችግር አለብን ክቡር ሚኒስትር?
- የዓለም የአየር ጠባይ ለማሻሻል በኪዮቶ የተደረሰውን ስምምነት ኢሚሽን መቀነስ ነው፡፡
- አዎን፡፡
- እናንተኮ እየቀነሳችሁ አይደለም፡፡
- እ...
- እየቀነሳችሁ አይደለም ብቻ ሳይሆን ለመቀነስም አትፈልጉም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ቻይና የአፍሪካ ወዳጅ ናት፡፡
- አፍሪካውያን በዚህ ስብሰባ በቻይና ላይም ቁጣ እያሳዩ ነው፡፡ ይህን ታውቃለህ?
- አይቻለሁ፡፡ ይህን ለማስወገድ እኮ ነው ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር የፈለግኩት፡፡ በነገራችን ላይ!
- በነገራችን ላይ ምን?
- በመንገድ ሥራ በግልገል ጊቤ ፕሮጀክት ቻይና ኢትዮጵያን ለመርዳት ከፍተኛ ዝግጅት እንዳደረገች ልነግርዎት እፈልጋለሁ፡፡ እንኳን ደስ አለን፡፡
- አልገባኝም?
- ቻይና ኢትዮጵያን ለመርዳት መዘጋጀቷን አለቆቼ ንገራቸው ስላሉኝ ነው፡፡ አሁን በስልክ ነግረውኛል፡፡
- የምናወራው ስለ "ክላይሜት ቼንጅ" መሰለኝ፡፡
- አዎን፡፡
- ቻይና ልትረዳን ነውና ዝም እንድንል ትፈልጋለህ?
- እኔ የተናገርኩት ወዳጅነታችንን ለመግለፅ ነው፡፡
- ወዳጅነታችንን ለማጠናከር በግልገል ጊቤና በሌላም ስለምታግዙን ዝም እንበል?
- ለአፍሪካ ካሳ ካልተከፈለ ቻይና ውሉን አትፈርምም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ አድርጉልን ለማለት ፈልጌ ነው፡፡
- ቻይና ራስዋስ ኢሚሽን ለመቀነስ ተስማምታለች? የግሎባል ዎርሚንግ ችግርን ለመፍታት ቆርጣ ተነስታለች ወይ? ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢጠይቁኝስ?
- ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር የቻይና ልዑካን ቡድን መሪ እየጠራኝ ነው፡፡ ይቅርታ እንገናኛለን፡፡
- እሺ ቻው፡፡
(ቻይናዊው መሄዱን አይቶ ከሕንድ ልዑካን አንዱ መጣ)
- ክቡር ሚኒስትር እኛ ራሳችንን ታዳጊ አገር ብለን ነው የምንወስደው፡፡ ችግራችን አንድ ነው፡፡ እኛ እጅ ለእጅ ተያይዘን መንቀሳቀስ አለብን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ጥሩ፡፡
- በነገራችን ላይ ክቡር ሚኒስትር እግረ መንገድህ ኢትዮጵያ ከሕንድ ምን እንደምትፈልግ አጥንተህ ና ተብያለሁ፡፡ ሕንድ ኢትዮጵያን ለመርዳት ተዘጋጅታለች፡፡
- የምትረዱን ስለሆነ ክላይሜትን በሚመለከት በእናንተ ላይ ያለን ወቀሳ እንተወው?
- እኛ ታዳጊ አገር ነን፡፡ ምን የሚያስወቅስ አለን ክቡር ሚኒስትር?
- የእናንተ የኢንዱስትሪ አሚሽን አደገኛ ነው፡፡ እናንተም በኪዮቶ ስምምነት መገዛት አለባችሁ፡፡
- ከሕንድ ጋር ጥንታዊ ግንኙነት የነበራት አፍሪካዊ አገር ኢትዮጵያ ናት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እና ይሄ ኢሚሽኑን ይቀንሰዋል?
(ከስብሰባው አዳራሽ ውጭ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አለ፡፡ አንዳንድ የሰልፉ ተሳታፊዎችም እየታሰሩ ነው፡፡ ግቢው ውስጥ ልዩነት የሰፈነበት የየቡድን ወሬ እየተጧጧፈ ነው፡፡ አዘጋጆቹ ስብሰባው ያለስኬት እንዳይበተን እየተሯሯጡ ናቸው፡፡ ምሳ ሰዓት ላይ ክቡር ሚኒስትሩ ባሉበት ጠረጴዛ አሜሪካውያንም አውሮፓውያንም አሉ)
- አሁን ጥሩ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ ፈረንሳይ የደን እንክብካቤን በሚመለከት አዲስ ሃሳብ ይዛ መጥታለች፡፡ ከእንግሊዝ ጋር ሆናም ለክላይሜት ቼንጅ ባጀት ይመደብ ብላለች፡፡ የዱሮ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አልጎር በሰሜን ዋልታ በረዶ እየቀለጠ እንደሆነ የሚያሳይ ፊልም ይዘው መጥተዋል፡፡ ብቻ ደስ ይላል፡፡
- ለአፍሪካ የሚከፈለው ካሳ በሚመለከትስ ምን አላችሁ?
- ክቡር ሚኒስትር አሁንኮ ችግሩ ማን ያዋጣ? ስንት ይዋጣ? የሚለው ለመወሰን እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው፡፡
- ምነው ባንኮቻችሁን ለመደጎም ይህን ያህል ጊዜ አልወሰደባችሁ? ማን ይደጉም? ስንት ይደጉም የሚለው ለመወሰን አይከብድም? ባንኮቻችሁን ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ በቢልዮኖች ደጉማችኋል?
- መሰጠቱማ አይቀርም፡፡ ሄላሪ ክሊንተን እዚህ አለች፡፡ ለኢንቫይሮመንት ያላት ትኩረት የታወቀ ነው፡፡
- በክሊንተን ጊዜ እኮ ነው አሜሪካ የኪዮቶ ስምምነት አልፈርምም ያለችው፡፡ ያኔኮ ቢል ክሊንተን ነበር ፕሬዚዳንቱ፡፡
- ባል ሌላ ሚስት ሌላ ናቸው?
- ያኔማ ሴናተር ነበረች ብዬ ነው፡፡
- ብቻ የበለፀጉት አገሮች ተሰብስበው ጥሩ ውሳኔ ያሳልፋሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
- አንዱ ተቃውሟችንኮ ይህ ነው፡፡
- ምኑ? ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ታዳጊ አገሮች የሌሉበት ለብቻችሁ የምታደርጉት ስብሰባና መመሳጠር ነው የጠላነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ውጤቱ ግን ያስደስታችኋል፡፡ አሁን ጥሩ ውሳኔ እንዲተላለፍ እያረቀቅን እንገኛለን፡፡ ውሳኔውን ስትሰሙት ትደሰታላችሁ፡፡
- ይህም ነው አንዱ ቅሬታችን፡፡
- ምኑ?
- ከእኛ ተደብቃችሁ አታርቅቁ፡፡ እኛም መሳተፍ አለብን፡፡ በውይይቱም በማርቀቁም አፍሪካን የሚያገል ሥራ አትስሩ?
- ከኢትዮጵያ ጋር ችግር የሚኖረን አይመስለንም፡፡ የአፍሪካ ወኪል ሆና ስለመጣች እንግባባለን፡፡ በነገራችን ላይ በቅርቡ ስለሰብዓዊ መብት እየቀረበ ያለው ሪፖርት ሙሉ በሙሉ አልተቀበልነውም፡፡ እናንተ እዚህ ደግፉን እኛም እዚያ እንደግፋችኋለን፡፡
- አልገባኝም?
- ክቡር ሚኒስትር ኢትዮጵያ እንዳትወገዝ እናደርጋለን ማለቴ ነው፡፡
- እናንተ ትደግፉናላችሁ፣ አታወግዙንም ብለን ኢሚሽን እንደፈለገው ይሁን፣ ካሳም አትክፈሉ እንበል፡፡
- እንዲያውም ከካሳው በላይ ለኢትዮጵያ እርዳታ እንዲሰጥና ተራበ የተባለው ስድስት ሚልዮን ሕዝብ ከሞት እንዲተርፍ እየተንቀሳቀስን ነው፡፡
- ስለዚህ ኢትዮጵያ ለክላይሜት ቼንጂ መሟገት ታቁም፣ አፍዋን ትዝጋ?
- አፏንማ አትዘጋም ለድጋፉም አፏ ይከፈት ማለታችን ነው፡፡
(ምሣውን መብላት አስጠላቸው፡፡ ትንሽ ቀማመሱና ሰላምታ ሰጥተው ሄዱ፡፡ በአቅራቢያቸው በሚገኘው ካፌ ቡና አዘዙ፡፡ እንደአጋጣሚ ኢትዮጵያዊት ወጣት ካፌ ውስጥ እያስተናገደች ነበር)
- ኢትዮጵያዊት ትመስያለሽ?
- ነኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ሚኒስትር መሆኔን እንዴት አወቅሽ?
- የሰላማዊ ሰልፉ አባል ነኝ፡፡ ተረኛ ስለሆንኩ እንዳያባርሩኝ መጣሁ እንጂ ስጨርስ እንደገና ሰልፉን እቀላቀላለሁ፡፡ አንዱ ሚኒስትር ናቸው ብሎ አሳይቶኛል፡፡
- እሺ፡፡
- ያሁኑ ዜና ግን አልገባኝም፡፡
- ምን የሚሉት ዜና?
- መሪዎቹ ከመምጣታቸው በፊት ሁሉም ግልፅ ይሆናል፡፡ ለስምምነት ዝግጁ እንሆናለን የሚል ዜና ነበር፡፡
- አልሰማሁትም፡፡
- ስብሰባው ውስጥ አብራችሁ አይደላችሁም?
- በአንዳንድ ጉዳይ ከእኛ ተደብቀው ተነጋግረው ይስማማሉ፡፡
- አያሳትፏችሁም?
- አንዱ ይህ ነው፡፡
- ምን ክቡር ሚኒስትር?
- "አሳትፉን" የሚል ጥያቄ ነው ያለን፡፡
- እናንተም "አሳትፉን" ትላላችሁ?
- አዎን ትልቁ ጥያቄያችን እሱ ነው፡፡ ምነው ሳቅ አልሽ?
- "አሳትፉን" ስትሉ ነዋ ገርሞኝ፡፡
- ለምን ይገርምሻል?
- ሚኒስትሮች አሳትፉን የምትሉ አይመስለኝም ነበር፡፡
- ይኸው እያልን አይደል?
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእናንተ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ባላችሁት ነበር ክቡር ሚኒስትር?
- ምን የሚል ጥያቄ?
- አሳትፉን!

girreda

Posts : 11
Join date : 2009-12-19
Age : 34
Location : Adama University

http://0914129948.ning.com

Back to top Go down

Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? Empty Re: Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Post by girreda Sun Dec 20, 2009 7:51 am

የኰፐንሃገኑ ጉባኤ በተደበላለቀ ስሜት ተጠናቀቀ
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በተባበሩት መንግሥታት ከተዘጋጁ ስብሰባዎች በትልቅነቱ ብዙ የተባለለት፣ የአፍሪካ 650 ሚሊዮን ሕዝብ ተስፋ የሰነቀበት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሌሎች ታዳጊ አገሮች ሕዝቦች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውና ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ከትናንት በስቲያ የተጠናቀቀው የኮፐንሀገኑ የአየር ንብረት ጉባኤ የተደበላለቀ ስሜት ፈጥሯል፡፡

ቀድሞም ድርድሩ ላይሳካ ይችላል የሚለው ጥርጣሬ ባየለበት ሁኔታ ውስጥ ሁሉንም ወገን ሊያስማማ የሚችል አቃፊ ሕግ ሳይወጣ ቀርቷል የሚል ብሶት በአንድ ወገን ሲያስተጋባ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ ለታዳጊ አገሮች እንደ መነሻ ሊሆን የሚችል የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ከማስቻሉም በላይ የዓለም ሙቀትን ለመቀነስ የሚያስችል ስምምነት ተፈጥሯል የሚል ድምፅ ተስተጋብቷል፡፡

ወትሮም ቢሆን በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ውድመትና የኢኮኖሚ መናጋት ስላደረሰባቸው ከዚህ ሰቆቃ ውስጥ ለመውጣት የበለፀጉ አገሮችን የገንዘብ ድጋፍ ሲሹ የነበሩት ታዳጊ አገሮች የተከፉ ይመስላሉ፡፡ የበለፀጉ አገራት ደግሞ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ወገን የሚያስደስት ስምምነት ላይ መድረስ አዳጋች በመሆኑ አሁን የተገኘው ውጤት እንደ ታሪካዊ ርምጃ መቆጠር ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የአፍሪካን የተደራዳሪዎች ልዑክ የመሩት ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሣይታሰብ አዲስ የመደራደሪያ ሃሣብ በማቅረባቸው ከአፍሪካ ሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ወቀሳ ቢያስነሳባቸውም፣ የሌሎችን ድጋፍ አላጡም፡፡ ቀድሞ ከነበረው አቋም ለየት ባለ ሁኔታ ባቀረቡት ፕሮፖዛል የበለፀጉ አገሮች አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋም እንድትችል ለመነሻ ያህል ከአቪዬሽን ከመርከብ ጭነት እና ከገንዘብ ተቋማት ከሚገኝ ታክስ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ የጠ/ሚኒስትሩ ፕሮፖዛል በእንግሊዝ ጠ/ሚኒስትር ጐርደን ብራውንና በፈረንሣዩ ፕሬዚዳንት ኒኰላስ ሳርኰዚ ይሁንታ የተሰጠው ሲሆን፣ ሌሎች የአውሮፓ አገራትም ድጋፋቸውን ቸረውታል፡፡ በፕሮፖዛሉ መሠረት ለድሀ አገሮች እ.ኤ.አ. 2010 እስከ 2012 በየዓመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ከዚያም ይኸው ገንዘብ ወደ 50 ቢሊዮን ከፍ እንዲልና ከ2020 በኋላ በየዓመቱ እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ይገኛል፡፡ ይህ የሚገኘውም የገንዘብ ድጋፍ በአፍሪካ ልማት ባንክ ሥር በሚቋቋም ባለአደራ ቦርድ እንዲመራ የሚጠይቅ ፕሮፖዛል ነው የቀረበው፡፡ የሚገኘው ገንዘብ የአየር ፀባይ ለውጡን ለመቋቋምና የካርቦን ልቀትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

የጠ/ሚኒስትሩን ሀሣብ የተቃወሙ የአፍሪካ ሲቪል ማኅበረሰብ ቡድን ግን የሚለው ቀደም ሲል ለመጠየቅ የታሰበውን 400 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚቀለብስና የአፍሪካን ድምፅ የማይወክል ነው ሲሉ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

"ያቀረብኩት ፕሮፖዛል የተወሰኑ አፍሪካውያንን ሊያስቆጣ እንደሚችል አውቃለሁ" ያሉት ጠ/ሚኒስትር መለስ፣ ፕሮፖዛላቸው ቀደም ሲል ከነበረው የመደራደሪያ ሃሣብ ለወጥ ማለቱንና ይህም የበለጠ አስተማማኝ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ሲባል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ "ከሌሎቹ የበለጠ እያጣን ነው በመሆኑም ግትር መሆን አይኖርብንም የበለጠ መጓዝ ይኖርብናል" ብለው በተፈጠረው ሁኔታ ተስፋ መቁረጥ ሣይሆን ሁሉንም የሚያስደስት ስምምነት ይኖራል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ያነጋገራቸው አንድ ከፍተኛ የአሜሪካን ተደራዳሪ የበለፀጉትም ሆኑ ታዳጊ አገራት የሚወስዱአቸው ብሔራዊ እርምጃዎች ላይ፣ ከ100 ዓመት በፊት የነበረው የዓለም ሙቀት ከ2 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ እንዳይጨምር ለመገደብ፣ አገሮቹ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን በተመለከተ መረጃ እንዲለዋወጡና ይህንንም ግልፅና ጥርት ባሉ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው የድርጊት መርሀ ግብሮች አማካይነት እንዲያስፈፅሙ ተስማምተዋል ብለዋል፡፡ ወደ 130 አገሮችን የሚወክለው ጂ77 የተባለው ቡድን ዋና ተደራዳሪ የሆኑት ሱዳናዊው ሚ/ር ሉሙምባ ዲ አፒንግ የተደረሰበት ስምምነት አልተዋጠላቸውም፡፡ "ይህ ስምምነት በአፍሪካና በትናንሽ ደሴት አገሮች ላይ ጥፋት ያስከትላል፡፡ የአገሮችን የፍላጐት መጠን ያሳነሰ ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጡን ለመቋቋም የታሰበውን ሁሉ የማይጨበጥ አድርጐታል" ሲሉ ነቅፈዋል፡፡

በእሳቸው አባባል የተደረሰው ስምምነት ታዳጊ አገሮችን የድህነት አዙሪት ውስጥ ይከረችማቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም በሳቸውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ መካከል ያለውን ልዩነት ሊያሣዩ አልቻሉም ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ተነሳሽነት ፌዴሬሽን መሪ የሆኑት ሚ/ር ኪም ካርስተንሰን በበኩላቸው ድርድሩ አልቋል ተብሏል፡፡ ነገር ግን ይህ ድርድር አለቀ ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡ ምክንያቱም መሪዎቹ የወሰኑት ውሳኔ እዚህ ጉባኤ ሳይመጡ የጨረሱትን ነው፡፡ "በመሆኑም ሁሉንም የሚያካትት የሕግ ማዕቀፍ ሳይወጣ ድርድሩ አበቃ ማለት ከፊታችን የበለጠ ፈታኝ ነገር መኖሩን ያሳየናል" ብለዋል፡፡

የአየር ንብረት ውይይት ዙሪያ በአድቮኬሲ ሥራ ላይ የተሰማሩት ሚ/ር ኔልሰን ሙፉህ በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ምክንያት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በዓለም ዙሪያ ይሞታሉ፣ ከነዚህም ውስጥ አብዛኛው የታዳጊ አገር ዜጐች ናቸው ብለው፣ "የበለፀጉ አገሮች በኰፐንሀገን ቁርጠኝነታቸውን አለማሳየታቸው የሟቾች ቁጥር የበለጠ እንዲያሻቅብ ያደርጋል" ሲሉ ተችተዋል፡፡

"ታሪካዊ" የተባለለት የኰፐንሀገኑ የአየር ንብረት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ብቸኛው አሸናፊ ሆነው እንዲወጡ አድርጓቸዋል የሚል ትችት ያስነሳ ሲሆን፣ አሜሪካ ዋነኛዋ የዓለም በካይ ናት የሚለውን ስሞታ ለማሰረዝ እና የድርድሩ አካል መሆኗን ለማሳየት የ100 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ብትገባም፣ በተናጠል ከሕንድ፣ ከቻይናና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያደረገችው ስምምነት ውዳሴ አላስገኘላትም፡፡

የዓለም ሙቀትን ከ100 ዓመት በፊት ከነበረበት ሁለት ዲግሪ ሴሊሺየስ እንዳያልፍ ለመገደብ ስምምነት መደረሱ በበለፀጉ አገሮች እንደ አዎንታዊ ርምጃ ቢታይም፣ የብዙ አገሮች ተወካዮች ይህ በቂ እንዳልሆነና አሁን የሚታየውን ችግር ሊፈታ እንደማይችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የተጠየቁ የበርካታ አገሮች ተወካዮች ፊታቸው ላይ ብስጭት ይታይ እንደነበር ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡

የኰፐንሀገኑ ስብሰባ ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስዷል፣ ይህም እንደ በጐ ጅምር ሊታይ ይገባል፣ በነዚህ ጅምሮች ላይ ወደፊት በርካታ ሥራዎችን መሥራት እንችላለን ያሉት የበለፀጉ አገሮች ሲሆኑ፣ ታዳጊ አገሮች ደግሞ የጠበቁትን ባለማግኘታቸው ግራ መጋባት ላይ እንዳሉ ለሁለት ሣምንታት በጭቅጭቅና በተለያዩ ሕዝባዊ ትዕይንቶች የተጠመደው ጉባኤ ዓርብ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተጠናቋል፡፡


girreda

Posts : 11
Join date : 2009-12-19
Age : 34
Location : Adama University

http://0914129948.ning.com

Back to top Go down

Did you know this? ይህን  ያውቁ  ኖርዋል  ? Empty Re: Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Post by Sponsored content


Sponsored content


Back to top Go down

Back to top


 
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum