Ethiopians Fun Forum.
Would you like to react to this message? Create an account in a few clicks or log in to continue.
Log in

I forgot my password

Who is online?
In total there are 5 users online :: 0 Registered, 0 Hidden and 5 Guests

None

[ View the whole list ]


Most users ever online was 156 on Mon Mar 15, 2021 10:19 am
New Sites
አዲስ ሳይት

ኢትዮ ሲንግልስ
Meet Ethiopians Singles | Register Now

ኢትዮ ፎረም
Ethiopians Forum
Latest topics
» Sh\\a Sex{wl
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyThu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyThu Oct 23, 2014 5:13 pm by nenash

» Sh\\a Sex{wl
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyThu Oct 23, 2014 5:12 pm by nenash

» Sxs Film Hindi
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyTue Oct 21, 2014 9:31 pm by nenash

» Kingdom Age Hack Tool V2.5
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyTue Oct 21, 2014 8:00 am by nenash

» Ore Wa Kanojo O Shinjiteru! 02 | Checked
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyMon Oct 20, 2014 3:57 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySun Oct 19, 2014 2:20 pm by nenash

» English Conversation With Tamil Meaning Pdf-adds
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySun Oct 19, 2014 2:17 pm by nenash

» Hide My Ip Activation Key 5.4
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySun Oct 19, 2014 11:14 am by nenash

» Windows 8 All Editions Activator.exe
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySat Oct 18, 2014 10:01 pm by nenash

» ?????? Anime Anime03 ?? ?? ?? ???? ?? Blu-ray?
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySat Oct 18, 2014 8:08 pm by nenash

» Rhcsa Rhce Red Hat Linux Certification Practice Exams With V
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySat Oct 18, 2014 6:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySat Oct 18, 2014 12:09 pm by nenash

» (2011) Emyumiem Emkazamagreat Download Fevrier French Girl 9
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptySat Oct 18, 2014 12:05 pm by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyThu Oct 16, 2014 1:20 am by nenash

» Download Jason Mraz I'm Yours Free
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyThu Oct 16, 2014 1:16 am by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyWed Oct 15, 2014 9:31 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyWed Oct 15, 2014 9:24 pm by nenash

» Aim Bot Bf 3 Download
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyWed Oct 15, 2014 9:23 pm by nenash

» [Most_popular]_tudung_bj_abg_opis_3gp-adds
"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " EmptyWed Oct 15, 2014 1:06 pm by nenash


"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . "

Go down

"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " Empty "ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . "

Post by yaredlove Mon Oct 05, 2009 11:24 pm

"ሥዕል አደገ፣ አላደገም . . . " 984-life-and-art

አቶ ሉልሰገድ ረታ፣ ከአርባ ዓመት በፊት ከአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት በ1969 ዓ.ም. ተመረቁ፡፡ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በስቴጅ ዲዛይነር ኃላፊነት ለሁለት ዓመታት ሠሩ፡፡ ከዚያ ወደ ሶቭየት ኅብረት ሄደው ለሰባት ዓመታት የሥነ ጥበብ ሙያ አጥንተው በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀቁ፡፡ ከዚያ መልስ በኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ለአሥራ አንድ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ለሠዓሊ ሉልሰገድ ረታ፣ ብርሃነ ዓለሙ ሥዕልን በሚመለከት ላነሳላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡


ሪፖርተር፡- ሥዕል ለማን ነው የሚሣለው?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሥዕል ሲጀመር ከነጥብ ነው፡፡ ከነጥብ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሄዱ መስመሮች ይገጣጠማሉ፡፡ ሥነ ጥበብ መጀመሪያ ለራሴ ነው፡፡ ምን ያህል ሥነ ጥበብን አውቃለሁ? ምን ያህል ተረድቼዋለሁ? ሥነ ጥበብ ምንድነው? ከታሪክ፣ ከባህል፣ ከኃይማኖትና ከቦታ መመንጨት አለበት፡፡ ሥዕል የዚህ ሁሉ ውጤት ነው፡፡ የአገር መልክ ስለሆነ የአገር ሐብት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ድርሰት አደገ ወይም አላደገም ብለን የተፃፉ መጽሐፎችን ከይዘትና ከቅርፅ አንፃር መርምረን መከራከር እንችላለን፡፡ ሥዕልስ አደገ ወይም አላደገም ብለን ምን ማስረጃ ይዘን ነው የምንከራከረው?

አቶ ሉልሰገድ፡- መከራከር ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ምን አለ? ይባላል፡፡ በየትኛውና በማን ሥራ ላይ እንከራከር? አከራካሪውና ተከራካሪውስ ማን ነው? ምን ተሠርቷል? ምን አልተሠራም? ምን ተሟልቷል? ምን አልተሟላም? ብሎ ይህንን የሚይዝ አካል መኖር አለበት፡፡ በሀገራችን ሥራው አለ፡፡ የሌለው ሒስ ነው፡፡ ሒስ በሌለበት እንደ አሸን የፈላውን የሥነ ጥበብ ሙያ ዛሬ አደገ አላደገም ብሎ ለመናገር ብቃቱ ያላቸው የተወሰኑ አሉ፡፡ ሥነ ጥበብ (በተለይ አርት) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ሥነ ጥበብ ልክ እንደ ቦክስ፣ ብስክሌት፣ እንደ አትሌቲክስ የግል ጥረትና የብዙሃን ተሳትፎ ውጤት ነው፡፡ በትምህርት ያገኘነውን፣ በልምድ ያካበትነውን፣ በዕውቀት አባዝተን (አልብሰን) እንደፈለግን ነፃ ሆነን መስጠት አለብን፡፡ በእኛ ሙያ አርቲስቱ ነፃ ነው ይባላል፡፡ ለምንድነው ነፃ ነው የሚባለው፡፡ ራሱን ለመግለፅ የሚያስችል በቂ ቴክኖሎጂ ስላለው ነው፡፡ ነፃነት ሲባል ጦር መዝዞ በቡድን ማሸነፍ አይደለም፡፡ ነፃነት ማለት እንደፈለግክ ዘፍነህም ይሁን አልቅሰህ፣ ሮጠህም ይሁን ተቀምጠህ ማሸነፍ ነው፡፡ እድሉ እኛው ጋ ነው ያለው፡፡ ሥራህን ማሳየት አለብህ፡፡ ጊዜ አልፎበት፣ ባለመቻል፣ ባልሆነ ነገር ላይ ተጠምዶ ሥራውን በአግባቡ የማያሳይ አለ፡፡ እደጉ ተመንደጉ የሚል ጠፍቶ አገራችን በሙያው እየቀጨጨች ነው፡፡ እኛ ባለቤት ነን፡፡ እንደ ባለቤትነቴ ስትጠይቀኝ የምመልስልህ አምኜበት ነው፡፡ ፈልጌ ነው እንጂ ተገድጄ አይደለም፡፡ ዛሬ አንተ የምትጠይቀኝ ጥያቄ አርባ ዓመት ያጠራቀምኩት ሙያዬ ውጤት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በድርሰቱ ሥራ ላይ ጥቂትም ቢሆኑ ሐያሲዎች አሉ እንበል፡፡ በሥዕሉስ እውቅና የተሰጣቸው አሉ?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሙከራው አለ፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነርሱም እዚህ አገር የሉም፡፡ ሒስ ራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነው፡፡ ሒስ ጥሩ ጎን አለው፡፡ የሚያነሳም የሚጥልም ነው፡፡ ዋናው መተኮር ያለበት ግን ግለሰብ ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን ነው፡፡ ስለሚወደኝ የሌለኝን እንዲሰጠኝ አልፈልግም፡፡ ባለው ላይ ምን ላሳይ እንደፈለግኩ፣ ዓላማዬ ምን እንደሆነ፣ ምን እንዳየ መናገር መቻል አለበት፡፡ ይሄ በትክክል ከተሠራ ለባለሙያውም ለሙያውም ይጠቅማል፡፡ አገራችን የምታድገውም እንዲህ ሲሆን ነው፡፡ ሒስ በሌለበት እስካሁን ቆይተናል፣ ወደፊትም እንቆያለን፡፡ እንዲሁ እየተያየን አንደኛ እገሌ፣ ሁለተኛ እገሌ እያልን የምንሄድበት ደረጃ ላይ አይደለንም፡፡ ሁላችንም የራሳችን መንገድ አለን፡፡ ዛሬ ከሆነልኝ ነገ ላይሆንልኝ ይችላል፡፡ ትልቁ ቁም ነገር መሥራት ነው፡፡ እኔ ሒስን አልጠብቅም፡፡ ሒስ ከጠበቅኩ ከቤቴ አልወጣም፡፡ እርሱ ስለሌለ ሥራዬን አላቆምም፡፡ ሒሱ ወደፊት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ዛሬ ትምህርት ቀላል ነው፣ የምትለፋበት አይደለም፡፡ እቤትህ ይመጣልሃል፡፡ ያሉት ሠዓሊዎች ውስንም ቢሆኑ እስካሁን የተደረገው ጥረት ቀላል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ የምትወዳደረው በዚህ ነው፡፡ በአፍሪካ ውስጥ እንዳሉት አይደለችም፡፡ አፍሪካ በቅርፅ ነው፡፡ የእኛ ለየት ይላል፡፡ በኃይማኖታችን፣ በባህላችን፣ በታሪካችን፣ በቋንቋችን፣ በጽሑፋችን ለየት እንላለን፡፡ ይሄ ሁሉ ትጥቅ እያለ በጥበብ ላይ እንደፈለግኩ መራመድ አለብኝ፡፡ በራሴ መተማመን አለብኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ሠዓሊው እየሣለ ደካማና ጠንካራ ጎኑን የሚያይለት ሐያሲ ከሌለ እድገቱ አስተማማኝ ይሆናል?

አቶ ሉልሰገድ፡- እኔ የምታውቀውን ትልቅ ሰው ጥራ ብትለኝ መጀመሪያ የምጠራልህ የአገሬን ሰው ነው፡፡ ትልልቅ ሰዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት እኛ ማዳበር አለብን፡፡ በራሳችን መኩራት ስንጀምር ከዚህ የበለጠ በራስ መተማመን የለም፡፡ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንሄዳለን፡፡ ሒስ የሚጠቅመው ሙያው እንዲያድግ እንጂ ሰውዬውን ለመምታት መሆን የለበትም፡፡ የእኛ አገር ብርድ እንደሌላው አገር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ነገር ኮስታራ ነው፡፡ ብርድ ከመታህ መታህ ነው፡፡ አያባብልህም፡፡ ፀሐይ ከሞቀህም በደንብ ነው፡፡ እናማርራለን፡፡ ለምንወደው ነገር ያለንን እንሰጣለን፡፡ በቀላሉ ደግሞ ሸብረክ እንላለን፡፡ እንደሌላው መተጣጠፍ አንችልበትም፡፡ እኛ ማየት ያለብን ካለው ሁኔታ ጋር እንዴት ማዛመድ እንችላለን የሚለውን ነው፡፡ መደማመጥ፣ መከባበር፣ መዋደድ ካልቻልን የትም አንደርስም፡፡ ሁሉም ትልቅ መሆንን ይፈልጋል፡፡ ትልቅ የሚያደርገው ግን ሥራ ነው፡፡ ሥነ ጥበብ መጀመሪያ ለራስ ነው፣ ከዚያ ለአገር ነው፡፡ ደስታውም እንደዚሁ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሥነ ጥበብ (አርት) አደገ ብለውኛል፡፡ ይህንን በምንድነው የሚያረጋግጡልኝ?

አቶ ሉልሰገድ፡- ይዘትና ቅርጽን ነው የሚይዘው፡፡ በቅርፅ ውስጥ ውስን ነገሮች አሉ፡፡ በሥነ ጥበብ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አንድ ባለሙያ እቤቱም ሆነ አደባባይ ያወጣቸውን ሥራዎቹን ስናይ ነው አደገ የምንለው፡፡ ያላደግንበት፣ ያልታየንበት ምክንያት ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ ማሳያ ቦታ የለንም፡፡ ጋለሪ የለንም፡፡ ዝም ብሎ ማየትና ማዳመጥ ብቻ አይደለም፡፡ አንድ ነገር ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውም እንግዳ መጥቶ ማየት አለበት፡፡ ወጣቱ እያየ ማደግ አለበት፡፡ ትልቁ ነገር ቦታ ነው፡፡ ሜዳው ካለ ሁላችንም እንጋልባለን፣ አገላለባችን ግን ለየቅል ይሆናል፡፡ የምንመረጥም የማንመረጥም እንኖራለን፡፡ በአገራችን፣ የአፍሪካ አገሮች የሚያዘጋጁት ዓይነት ዝግጅት አለመኖሩ ያጎድልብናል፡፡ በደቡብ አፍሪካ፣ በሴኔጋል፣ በግብጽ የሚካሄዱ የአፍሪካ የሥዕል፣ የግጥም፣ የሲኒማ ዝግጅቶች ባህልን ለመለዋወጥ ይጠቅማሉ፡፡ በሌላ በኩል ዘርፉ እንዲያድግም አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ዝግጅት እዚህ እናድርግ ብንል የትኛው አዳራሽ ውስጥ? ከባድ ነው፡፡ ይህንን የሚያስብ አካል መኖር አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- እንደሌሎቹ የሙያ ማኅበር የላችሁም፡፡ ለምንድነው?

አቶ ሉልሰገድ፡- የለንም፡፡ ለምን እንደሌለን ምላሽ አልሰጥህም፡፡

ሪፖርተር፡- ስለ መጽሐፍ ማንበብና መፃፍ የሚችል፣ ስለ ሙዚቃ ደግሞ ማዳመጥ የሚችል የመሰለውን አስተያየት መስጠት ይችላል፡፡ ሥዕልን በሚመለከት አስተያየት የሚሰጠው ማን ነው? ተመልካቹስ ማን ነው?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሥዕልን የሚመለከተውማ ሕዝብ ነው፡፡ ሌላ ማን አለ? በአሁኑ ሰዓት ወጣቱም፣ መካከለኛውም፣ አዛውንቱም ለሥዕል ፍቅር ያለው ኤግዚቢሽን ሲዘጋጅ ያያል፡፡ ሃሳብ ተለዋውጦ፣ ተመካክሮ፣ ተከራክሮ ይመለሳል፡፡ እንዲህ ነው የሚጀመረው፡፡ አንድ ሰው፣ የእገሌ ዘፈን ጥሩ ነው፣ መጥፎ ነው የሚለው ሰዎቹን ስለሚያውቃቸው ነው፡፡ እኛ ውስን ነን፡፡ በሰው ዘንድ የሚታወቁ የተወሰኑ ናቸው፡፡ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ጀምሮ እነ ታደሰ መስፍን፣ አለፈለገ ሰላም፣ አብዱራህማን ሸሪፍ፣ ወርቁ ማሞ፣ ወርቁ ጎሹ፣ ታደሰ በላይነህ አዲስ አይደሉም፡፡ የምናሳይበት ቦታ የለም፡፡ ባለሃብት ቢሠራልን እኮ ገቢ ያገኛል፡፡ በየሣምንቱ፣ በየወሩ የአንዱ ሠዓሊ ቀን እየሆነ እየተማረም ገንዘብ እየተገኘም ትልቅ ነገር መሥራት ይችላል፡፡ እምቅ ሃብታችንን የምናሳይበት መድረክ ሊኖር ይገባል፡፡ የሚያይ ሰው አልጠፋም፡፡ ማሳያ ቦታ ነው የጠፋው፡፡ አንድ የሥዕል ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት ትልቅ ወጪ አለው፡፡ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ፣ ጀርመን ጎቴ ኢንስቲትዩት፣ ጣሊያን ካልቸር፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥነ ጥበብ ማዕከል፣ አስኒ ጋለሪ፣ ለሥነ ጥበብ ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል፡፡ በቡድን ሆነው ጋለሪ ከፍተው ሥዕል የሚያሳዩም አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- አንድ ሠዓሊ ሥዕሉን ሲሥል ማንን ማዕከል አድርጎ ነው፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰቡ ክፍሎች፣ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉት ወይስ ባለ ሀብቶችን?

አቶ ሉልሰገድ፡- ከአንድ እርምጃ ነው መጀመር ያለብን፡፡ ሠዓሊውና ሸራው ከተገናኙ፣ በእሱ አስተሳሰብ አንድ ሠዓሊ የራሱ መግለጫ ዘዴ ካገኘ ያ ሥዕል ነው፡፡ የሚሠራቸው ሥራዎች ያዘሏቸው ቁም ነገሮች አገሪቱን የሚወክሉ ከሆኑ፣ ዓለምን የሚያግዙ ከሆኑ ሥዕል ነው፡፡ በየቦታው የምታየው ዲዛይን ከሥዕል ነው የሚነሳው፡፡ ሁሉም ነገር የራሱ ይትበሃል አለው፡፡ የምንገናኝበት መድረክ አለ፡፡ ያ መስመር ነው፡፡ መስመሮች ደግሞ ይለያያሉ፡፡ ወደ ላይ ከቆመ የሚተኮስ፣ ወደ ጎን ከሆነ የሞተ መሆኑን፣ ዚግዛግ ከሆነ አየር መኖሩን መሄድ መቻሉን ሞገድ መሆኑን መናገሪያ ነው፡፡ እነዚህን ማገናዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሥዕል መስመርና ነጥብ ብቻ ሳይሆን ቀለምም ይወስነዋል፡፡ መገለጫው ብዙ ነው፡፡ ቁሳቁስ፣ መልክዓ ምድር፣ አልባሳት፣ ኪነ ሕንፃ፣ ወዘተ. መጀመሪያ የምንሰራውን ማወቅ ነው፡፡ ሥዕል የሚሳለው ለሕዝብ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ ማንን አስበው ነው የሚሥሉት? ሠዓሊ የሚባለውስ ማን ነው?

አቶ ሉልሰገድ፡- ከመልክዓ ምድር፣ ከልብሳችን፣ ከመልካችን፣ ከቀለማችን፣ ከአካባቢያችን ጋር መተዋወቅ አለብን፡፡ ማዛመድ መቻል አለብን፡፡ የማዛመድ ክህሎታችን ጎልቶ የሚወጣው እንዲህ ስንነጋገር ነው፡፡ ብቃት ያስፈልጋል፡፡ እኔ የማስበውን ሳይሆን የማውቀውን ነው የምነግርህ፡፡ የማስበውን በሥዕል እንኳ አልሠራም፡፡ ምን ያህል በእኔ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ፣ እኔ ደግሞ ሌላውን አሳምናለሁ በሚል በራሴ ኃይል፣ በራሴ ቋንቋ፣ ባገኘሁት ዕውቀት ሥዬ ሕዝብ አስተያየት መስጠት መቻል አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- ሥዕል የሚገዙት በአብዛኛው የውጭ አገር ሰዎች ናቸው ሲባል እንሰማለን፡፡ የገንዘብ አቅም ስላላቸው ለእነርሱ ነው የሚሳለው?

አቶ ሉልሰገድ፡- ለምን ብለን ስንጠይቅ አፍራሽ እንዳይሆን፡፡ ከዚህ በፊት ሥዕልን ደፍሮ የሚገዛ ብዙም ኢትዮጵያዊ አልነበረም፡፡ አሁን ግን በስሜት ሊሆን ይችላል፣ በፍቅር ሊሆን ይችላል፣ በመፀፀት ኢትዮጵያዊም ይገዛል፡፡ የውጭ ፖስተሮችን ከመለጠፍ በአገሩ ልጅ የተሣለ ሥዕል መስቀል አስፈለገው፡፡ ትምህርት ቤት ገብቶ ግዛ አልተባለም፡፡ ስላየ፣ ስላሰኘውና ስለፈለገ ነው፡፡ ደስ ሳይለው ሠዓሊውን ለመርዳት ብሎ የሚገዛ ከሆነ፣ ከግድግዳ ላይ ሊያወርደው ነው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ማለት አይደለም፡፡ አሁን ኢትዮጵያዊውም ይገዛል፡፡ የሚፈለገውም ይኼ ነው፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ሥዕል መግዛት ጀምረዋል፡፡ ይሄ ትልቅ እድገት ነው፡፡ ልንኮራ ይገባል፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ እንደ አጀማመሯ አፍሪካ ውስጥ በሥነ ጥበብ ስሟን ማስጠራት አልቻለችም፡፡ ለምን?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሙያህን ማበልፀግና ማሳደግ ያለብህ አንተ ነህ፡፡ መንግሥትን መጠበቅ የለብህም፡፡ የተገኘ እድል በጋራ መጠቀም አለብን፡፡ ወደ ውጭ ሄዶ ልምድ ለመጋራት በመንግሥት ደረጃ ከሆነ በጀት መመደብ አለበት፡፡ በግል ግን እኔ ልሄድ እችላለሁ፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገሮች ይዘለላሉ፡፡ የምንሠራው ለአገራችን ስለሆነ በጀትም መኖር አለበት፡፡ ከዚያ በላይ ከሆነ ወደ ሌላ መሄድ ነው፡፡ ይህንን ዘመን መጠቀም አለብን፡፡ አንድ ቀን ፈንጥቀን እንወጣለን፡፡ ብዙ ተአምር የሚታይበት ዘመን እንደሚመጣ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሙያ ላይ መበልፀግ አለብን፡፡ ከችሎታዬ በላይ ብትቀባኝ አይጠቅመኝም፡፡ በሠራሁት መጠን ማበረታታት አለብህ፡፡

ሪፖርተር፡- ሥዕል የማዕረግ ስም አለው?

አቶ ሉልሰገድ፡- በአገሪቱ ያሉ ተቋሞች ይህንን አጥንተው ቢናገሩ መልካም ነው፡፡ በሥዕል ሎሬት ደረጃ ለመድረስ ምን ምን ማሟላት አለበት? ሕዝባዊ ሠዓሊ፣ ዓለም አቀፋዊ ሠዓሊ ልትባል ትችላለህ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልን እያደግን ነው መምጣት ያለብን፡፡ በእኛ አገር ስም መስጠት፣ መሸለም መቻል አለበት፡፡ ቋንቋው አይቸግርም፤ የሚቸግረው ሸላሚው ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የሥዕል ስም ሲጠራ ቶሎ ስማቸው የሚነሣው የአገራችን ሠዓሊዎች ምን ዓይነት የአሣሣል ስልት በመከተላቸው ነው?

አቶ ሉልሰገድ፡- አብስትራክት፣ ሪያሊስቲክ አርት አለ፡፡ አብስትራክት አርት ስውር ሥራ ይባላል፡፡ ምስጢር አዝሎ ቁም ነገርን የሚያስተላልፍ ነው፡፡ ሪያሊስቲክ ግልፅ ሥዕል ነው፡፡ ኮላሽ የተለጣጠፈ ሥራ ነው፡፡ በመስተዋት ላይ የምትሠራው ሥዕል አለ፡፡ ሞደርን አርት በተለያየ ቴክኒክ የምትገልጽበት ነው፡፡ አኒሜሽን፣ ስታሌሽን (ከቅርጽ፣ ከወዳደቁ ነገሮች) በአንድ ክፍል ኢሜጅ ፈጥረህ የምትሰራበት ነው፡፡ ግራፊክ አርት፣ ፔንቲንግ አርት አለ፡፡ ቅርጽ አለ፣ ሚዩራል አለ፡፡ ሚዩራል በሞዛይክ የሚሰሩ የግድግዳ ሥዕሎች ማለት ነው፡፡ ሞንሜንታል፣ አሊስትሪሽን የሚባሉ አሉ፡፡ በውስጡ ብዙ ነገር የያዘ ነው፡፡ ለሐውልት፣ ለአደባባይ ወዘተ. የሚሆኑ ሥዕሎች አሉ፡፡ እነዚህን ካላወቅን፣ ካላሳወቅን እኛም ካልተናገርን እንዲሁ እየተፃፈ ይቀራል፡፡ የእኛ ሰው ባለመጠየቁ፣ ብዙ ነገር ያመልጠዋል፡፡ መጠየቅ አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- የአገራችን የሥዕል ተመልካች የትኛውን የሥዕል ቴክኒክ ነው የሚስበው?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሞደርን አርት

ሪፖርተር፡- በሥዕል ሕዝብን መቀስቀስ፣ ማነሳሳት፣ ማሳመጽ ይቻላል? ከተቻለ የትኛው ሥዕል ሕዝብን ቀሰቀሰ? አሳመፀ?

አቶ ሉልሰገድ፡- በሥዕል መቀስቀስ አይቻልም፡፡ በሥዕል ማሳየት ነው፡፡ ቅስቀሳ የሚያስፈልገው ከሆነ በፖስተር ነው፡፡ ሕዝብ ለምን ያምፃል? በመጀመሪያ ደረጃ ማመፅ የለበትም፡፡

ሪፖርተር፡- ያመፀን ሕዝብ አመፁን እንዲያቆም በሥዕል ማግባባት ይቻላል?

አቶ ሉልሰገድ፡- ምንም ነገር ይሁን ምን ጋለሪዎች፣ ሥዕል ማሳያ የተለያዩ ቦታዎች ከሌሉ ሰብስበህ የምትናገረው አይደለም፡፡ የሠዓሊው ሥራ ና ተመልካች መገናኘት አለባቸው፡፡ ይህ መድረክ ካልተፈጠረ ችግር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በዓሉን እንዲጠፋ ያደረገው ኦሮማይ የተባለው መጽሐፍ ነው፡፡ ልክ እንደ ኦሮማይ መጽሐፍ ሥዕል ሥሎ የተሰደደ፣ ከአገር የወጣ፣ የታሠረ፣ እርምጃ የተወሰደበት ሠዓሊ አለ?

አቶ ሉልሰገድ፡- እንደዚያ ደፍሮ የሠራ የለም፡፡ ሥዕል እኮ ዲሲፕሊን ነው፡፡ ማመጽ፣ ፖለቲካ መናገር፣ መሳደብ ይቻላል፡፡ ማሳመጽና ማነሳሳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ማንን ነው የሚጠቅመው?

ሪፖርተር፡- ሕዝቡ ተጨቆንኩ ብሎ ሲያምን . . .

አቶ ሉልሰገድ፡- እሱ ፖስተር ላይ ይቻላል አልኩህ እኮ፡፡ ባለፈው መንግሥት ጊዜ ተጠቅመንበታል፤ ነገር ግን ማንን ጠቀመ? ፍላጎት ፖስተር መሆን የለበትም፡፡ ፍላጎት አርት መሆን አለበት፡፡ መፈለግ አለመፈለጉን በውስጥ ትናገራለህ፡፡ ብሶት፣ ጀግንነት፣ ውህደት፣፣ አንድነት፣ ጥል ወዘተ. አለ፡፡

ሪፖርተር፡- ሠዓሊው ያስተላለፈው መልዕክት በትክክል ሕዝብ ዘንድ ይደርሳል?

አቶ ሉልሰገድ፡- ሠዓሊው ከሚያየው ነገር ነው፡፡ ፍቅር፣ ሰላም፣ ብጥብጥ . . . አንዱ የሰው አንገት በጎራዴ ሲበጥስ አይቶ የሳለው ሳሎን ላይ ይሰቀላል?

ሪፖርተር፡- ሳሎን ባይሰቀል፣ ሙዚየም ውስጥ አይቀመጥም?

አቶ ሉልሰገድ፡- እሱ ሌላ ነው፡፡ ቀስቃሽ ሥዕሎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ሪያሊዝም የሕልም ሥራ ነው፡፡ የማታየውና የማትጨብጠው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ካርቱኖች አሉ፡፡ ብሶት መናገሪያ ናቸው፡፡ ያ ሥዕል አይደለም፤ መግለጫ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ገጣሚ፣ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ማስታወሻ ይዞ ሊገጥምና ሊጽፍ ይችላል፡፡ ሠዓሊስ?

አቶ ሉልሰገድ፡- በስኬች ያስቀምጣል፡፡ የሕይወት ትጥቅ ያስፈልጋል፡፡ አሻራ፣ ሜንቶር ያስፈልግሃል፡፡ የምታየው፣ የምታመሰግነው ሰው መኖር አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- ሠዓሊ መሠረት አድርጎ የሚሠራው የሚያየውን ወይስ የሚያስበውን?

አቶ ሉልሰገድ፡- በሚያየው ነው፡፡ የምናየውን ነገር እንዴት ነው ገልብጠን የምናየው? የምናየው ነገር ለእኛ ምን መልክ ይሰጠናል? በውስጡ ምን አዝሏል? አንዲት የተራበች ሴት ባይ ሥሥላት ብርቱካን ነው የማስይዛት፡፡ ምክንያቱም ሕይወት እንዲኖራት፣ መቀጠፍ እንደሌለባት ለማሳየት፡፡
yaredlove
yaredlove
Admin

Posts : 52
Join date : 2009-07-12
Age : 31
Location : Ethiopia/Nazareth

http://www.yared.tk

Back to top Go down

Back to top

- Similar topics

 
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum